• ETHIOPIAN PHOTOGRAPHY
You are here

አየር መንገዱ የአፍሪካ የዓመቱ የካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

አየር መንገዱ የአፍሪካ የዓመቱ የካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ የዓመቱ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ።

አየር መንገዱ ሽልማቱን ያገኘው በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ በተካሄደ የአፍሪካ አየር መንገድ ካርጎ ጉባኤ ላይ ነው።

የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፥ ሽልማቱ አየር መንገዱ በዘርፉ የሚሰጠውን አገልግሎት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

አቶ ተወልደ እንዳሉት፥ አዲስ አበባን አፍሪካን ጨምሮ የአውሮፓ፣ እስያ፣ የአሜሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የአየር ካርጎ መዳረሻ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

አየር መንገዱ በርካታ ሽልማቶችን ያሸነፈ ሲሆን፥ በተያዘው ዓመት በአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ ሽልማትንም ማሸነፍ ችሏል።

ከዚህ ባለፈም በተጓዦች የዓመቱ ተመራጭ አየር መንገድ በመባል ተሸላሚ መሆኑም ይታወሳል።
ምንጭ፦ wolfganghthome.wordpress.com

Related posts