ለመጀመሪያ ቀን የፍቅር ቀጠሮ የሚረዱ ምክረ ሃሳቦች

ለመጀመሪያ ቀን የፍቅር ቀጠሮ የሚረዱ ምክረ ሃሳቦች

ከብቸኝነት ህይዎት ተላቆ ጥንድ ለመሆንና ለመጣመር ከአቻ ጋር መተዋወቅና መግባባት ያስፈልጋል።

ከመግባባት ባለፈ የፍቅር ጓደኝነት በመመስረት በትዳር መጣመርና በጋብቻ መተሳሰርም ቀጣዩ የጉዞ ምዕራፍ ነው።

በዚህ ሂደት ለማለፍ አጣማሪየ ይሆናል ያሉትን መግባባት ወሳኝ ነው፤ ለመግባባት ደግሞ መተዋወቅ።

ለትውውቅ የመጀመሪያ የሆነው የመጀመሪያ ቀን ቀጠሮ ምን መምሰል አለበት የሚለው ጉዳይ ደግሞ የብዙዎቹ ጥያቄ ነው።

የስነ ልቦና ባለሙያዎች ደግሞ የመጀመሪያ ቀን የፍቅር ቀጠሮ የሚረዱ ምክር ሃሳቦችን አስቀምጠዋል፤

ቅድመ ዝግጅት ማድረግ፦ ምን ጊዜም ቢሆን የትኛውም ቀጠሮ ቅድመ ዝግጀት ይፈልጋል ስለዚህ ከዚህ አንጻር መዘጋጀቱ መልካም ነው።

በመጀመሪያ ስለምትገናኙበት ቦታ፤ የቀጠሮ ቦታ መገናኘት ይሻላል ወይስ የሆነ ቦታ ተገናኝቶ ጊዜያችሁን ወደ ምታሳልፉበት ቦታ አብሮ መሄድ።

ስለምትገናኙበት ቦታ ጠቋሚ አቅጣጫ ስለመኖሩ እንዲሁም የምታገኙትን ሰው የአመጋገብ ሁኔታ እና ምርጫ የሚያሟላ ስፍራ ስለመምረጣችሁም ማሰብ ይኖርባችኋል።

አዲስ ትውውቅ እንደመሆኑ መጠንም በማይከብድ መልኩ በጥሩ ሁኔታ ለመግባባት መሞከሩም መልካም ነው።

ምግብ ቤት ጎራ ስትሉም በተቻለ መጠን የቤቱ ኮሪደር ላይ የቤቱን ሙሉ ገጽታ ማየት በሚያስችል ስፍራ ላይ ብትሰየሙም በግልጽ ለማውራት እድልን ይፈጥራል።

የቀጠሮ ቦታ ምርጫ፦ የመጀመሪያ ቀን እንደመሆኑ መጠን ቢቻል በጣም ወሬ ያልበዛበት ቢሆን ይመረጣል።

ካለመተዋወቅና ከሌሎችም እንግዳ ስሜቶች የሚመነጨው አጋጣሚ በወሬ መሃል ያንን ሰው ብዙም እንዳይረዱት የማድረግ አቅም እንዳላቸውም ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከተቻለና አጋጣሚው ካለ የሙዚቃ ድግስ ያለበት ቦታ በመታደም ከዚያ በኋላ ያሉትን ጊዜያት ሻይ ቡና እያላችሁ ማሳለፍ።

ባለሙያዎቹ የዚህ አይነት አጋጣሚ ስለዛ ሰው የተወሰኑ ለመረዳትና ቀጥሎ በሚኖረው የሻይ ቡና ሰዓት ጥሩ መግባባትን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ይናገራሉ።

ስልክን አለመነካካት፦ ነገ አጣማሪየ ትሆናለች/ይሆናል ብለው በመጀመሪያ ቀን ቀጠሮ ያገኙት ሰው ጋር ጊዜ እያሳለፉ አሁንም አሁንም ስልክን መነካካት አላስፈላጊው ነገር ነው።

ይህን ማድረጉ አብሮ ላለ ሰው ክብር መንፈግ እና ምቾት እንዳይሰማው ማድረግ መሆኑንም ነው ባለሙያዎቹ የሚናገሩት።

አብረው ሆነው ሜሴጅ መላላክ አልያም መደዋወል በቀጠሮው ደስተኛ አለመሆንን መግለጫ ስለሚመስል ይህን ባያደርጉ ይመረጣል።

ከዚያ ይልቅ ላገኙት ሰው ሙሉ ትኩረትን መስጠትና አጋጣሚውን ልዩ ማድረግ የሚያስችሉ መንገዶችን መፍጠር ላይ ያተኩሩ፤ ስልክ መደወል ከፈለጉም ከቀጠሮው በኋላ ይከውኑት።

የሚያጫውት ርዕስ መምረጥ፦ ብዙ ጊዜ ቀላልና “አወ” ወይም “አይደለም” የሚል ምላሽ ያላቸውን ጥያቄዎች አለመጠየቅ በዚህ ጊዜ ይመከራል።

ከዚያ ይልቅ ሰፋ ያለ ውይይትን የሚያመጡ ርዕሶችን በመምረጥ መጠያየቅና መጨዋወቱ ይበልጥ ለመግባባትም ሆነ ስለዛ ሰው ማንነት በደንብ ለመረዳት ያግዛሉ።

ምናልባት ወቅታዊና የሆኑ አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ፣ ስለ ህይዎት ተሞክሮ እና ስለ አንዳንድ አጋጣሚዎች መጨዋወትንም ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ጥሩ አድማጭ መሆን፦ በምንም ርዕስ ቢሆንና በጣም በሚያውቁት ጉዳይ ላይ እንኳን ቢሆን በተቻለ መጠን ጥሩ አድማጭ ለመሆን ይሞክሩ።

ሲያዳምጡ ነገሮችን የተቀበሉበትን መንገድ አልፎ አልፎ በሰውነት እንቅስቃሴ መግለጽና እነዚያን ማብራራትም ይልመዱ።

ምናልባት የቀጠሯችሁ ሰዓት ካለቀም ደስ የሚልና ሊደገም የሚገባው ቆይታ እንደነበራችሁ በግልጽ መናገርና ለነበረው ጊዜ ማመስገንም መልካም ነው።

ሲለያዩም የስንበት ሰላምታን መስጠትና ሌላ ጊዜ እንደምትገናኙ መነጋገርንም ይልመዱ።

ታማኝ መሆን፦ አለመዋሸት እና ታማኝ መሆን በሰዎች ዘንድ ተቀባይነትን ለማግኘት የመጀመሪያው መንገድ ሳይሆን አይቀርም።

በመጀመሪያ የፍቅር ትውውቅ ቀጠሮ ቀንም ሳይዋሹ ታማኝ መሆን ለዘለቄታዊ መሰረት ነው።

ስለ ራስዎ፣ ስለ ስራዎ፣ ስለ ሚወዱት እና ስለሚጠሉት ነገር እና ስለ ሌሎችም ነገሮች በግልጽ ውሸት ሳይቀላቅሉ መናገር።

የሰውነት እንቅስቃሴዎን ይቆጣጠሩ፦ በቀጠሮ ወቅት ሰዎች የሚያሳዩት የሰውነት እንቅስቃሴ በተለያየ መልኩ ትርጉም ይሰጠዋል።

ከዚህ አንጻር ሲያወሩም ሆነ ሲያዳምጡ የሚተገብሯቸውን የሰውነት እንቅስቃሴዎች መቆጣጠርና በተቻለ መጠን አብሮዎት ያለውን ሰው ስሜት መጠበቅ ይኖርብዎታል።

በተቻለ መጠን እጅን አለማጣመር፥ ይህ ሲሆን በነገሮች እንደተሰላቹና ቀጠሮውን እንዳልወደዱት ማሳያ ነውና ያንን ያስወግዱ።

ማሽኮርመም፦ ሳይበዛ አልፎ አልፎ ትንሽ ማሽኮርመሙም መልካም መሆኑን ነው ባለሙያዎች የሚመክሩት።

ይህን ማድረጉ ለጨዋታ ያለዎትን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የእርስዎን ነገር በጨዋታ መልክ ለሰዎች ለማጋራትም እድልን ይፈጥራል።

አብረው እያሉ በአይን መጫዎት፣ ፈገግታ እና ውስን በሆነ ሁኔታ አካላዊ ንክኪ (እጅን በመያዝ) ሃሳብ መለዋወጥ።

እንደ ባለሙያዎች ይህን ሲያደርጉ ቀጠሮውን ቀላልና የማይከብድ በማድረግ መልካም መግባባትን ይፈጥራሉ።

ከዚህ ባለፈ ከሁኔታው ጋር የሚሄድ እና ብዙም ያልተጋነነ ቀለል ያለ አለባበስ ቢኖርዎት ይመረጣል።

የእርሷን/እርሱን ትኩረት አገኛለሁ በሚል እሳቤ ግን ከልክ በላይ መሽቀርቀርና መዘነጡም ያን ያክል አስፈላጊ አይደለም።

በተቻለ መጠን ቀለል ያለና የማይከበድ አለባበስ ቢኖርዎት መልካም መሆኑን ባለሙያዎች ይመክራሉ።

ወደ ቀጠሮ ቦታ ከማምራትዎ በፊትም ለራስዎ ትንሽ ጊዜ መስጠትና ዘና ለማለት ለሞክርንም ይልመዱ።

ስለ ሁኔታው እያሰቡ እንዳይጨነቁ ዘና ባለ መንፈስ ወደ ስፍራው ለማምራት ተረጋግተው ጊዜ መውሰድና ወደ ስፍራው ማቅናት።

ነቃ ለማለት ብለው ከቀጠሮ በፊት እንደ ቡና አይነት ትኩስ መጠጦችን አይሞክሩ፤ በጣም ስለሚነቁ ለትኩረት መልካም አይደለምና።

ከዚያ ይልቅ እንደ ሻይ ያሉ ትኩስ ነገሮችን መውሰድን ይልመዱ።

ምንጭ፦ howstuffworks.com/

Related posts